Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይሰራል-አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ በክልሉ ባለፉት አምስት አመታት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በዚህ ወቅት÷ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ፓርቲው ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠትና ፕሮጀክቶችን አቅዶ በፍጥነት በመተግበር እና ወደ ስራ በማስገባት ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን እያደረገ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑንም አንስተዋል።

መድረኩ በክልሉ አመራር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር የመፈፀም አቅምን ይበልጥ ለማጎልበት ትልቅ አስተዋፅፆ የሚኖረው መሆኑ መገለፁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በአሶሳ ከተማ በተካሄደ ተመሳሳይ መድረክ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን እንዳሉት÷ በክልሉ የነበረውን ያለመረጋጋት ችግር በጥበብና በበሳል አመራር ሰጪነት በመፍታት በሁሉም አካባቢዎች ሰላም ማስፈን ተችሏል፡፡

በኢኮኖሚ ጠንካራ ማህበረሰብ ለመፍጠር በተሰራው ስራም ከአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተጀመሩ ኤኒሼቲቮች አፈጻጸም የሚበረታታ ነው፤ በቀጣይ የቤተሰብን ብሎም የሀገርን ብልፅግና ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ያለፉት የለውጥ ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም ልማት፣ በተቋማት ግንባታ፣ በከተሞች እድገትና በሌሎችም ዘርፎች የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚነትና ምርታማነት ለማሳደግ አመርቂ ውጤቶች የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.