Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ በደረሰ የትራክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ጉዶ ባህር አካባቢ ትናንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

 

አደጋው በአካባቢው ትናንት 11፡30 የህዝብ ማመላለሻ መኪና መስመር በመሳት በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡

 

በአደጋውም እስካሁን የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአማራ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.