Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ እና አትሌት ሩቲ አጋ በ2025 የሺያሚን የማራቶን ሩጫ ውድድር ሪከርድ በመስበር አሸንፈዋል፡፡

በዢያሜን ማራቶን 2025 የወንዶች ሩጫ ውድድር አትሌት ዳዊት ወልዴ 2:06:06 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀደም ሲል የተያዘውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፏል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አሰፋ ቦኪ ደግሞ ውድድሩን በ2፡06፡32 በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በዚሁ ውድድር በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ ሶራ ውድድሩን 2፡18፡46 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አዲስ ሪከርድ መስበሯ ተሰምቷል ፡፡

በተጨማሪም በውድድሩ ጉተሜ ሾኔ 2:23:11 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ አትሌት ፍቅርተ ወረታ 2:23:15 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዛለች ፡፡

በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ በቻይና ሆንግ ኮንግ-ዙሃይ-ማካው ድልድይ በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር 1፡1፡27 በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.