Fana: At a Speed of Life!

የባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባሌ ሮቤ ያስገነባውን የዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልን አስመረቀ።

 

በምረቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ የቱሪስት መዳረሻ በሆነው የባሌ ዞን ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ይህ ተርሚናል የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳለጥ ከሚኖረው ሀገራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ለደንደበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

 

የኢትጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ  14 ሳምንታዊ በረራዎችን እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.