Fana: At a Speed of Life!

ኮምቦልቻ ከተማ የ22 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ለኮምቦልቻ ከተማ 22 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

ወ/ሮ ዓይናለም በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ሕይወት መለወጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡

ድጋፉም በከተማዋ የሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎችን ኑሮ ለማቃናትና የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ለመደገፍ እንደሚውል መናገራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.