ባሕርዳር ከተማና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ሙጂብ ቃሲም ባስቆጠራት ግብ እስከ ጨዋታው መጠናቀቂያ ድረስ መምራት ችሎ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ አሕመድ ረሺድ 88ኛው ደቂቃ ላይ ኳስ ከመረብ በማሳረፍ ድሬዳዋ ከተማን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ያደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ቢኒያም ፍቅሬ እና አብዶ ሳሚዮ በ23ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
በአንጻሩ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ አቤል ሃብታሙ ከመረብ አሳርፏል፡፡