Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ ያስገነባው የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል በከፊል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባበቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሕክምና ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታሉ ያስገነባው የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል በከፊል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባበቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሕክምና ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በከፊል ሥራ የጀመረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻሽል ገልጸዋል።

ማዕከሉ ኢትዮጵያን የሕክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትርጉም ያለው ድርሻ እንደሚኖረውም ነው ያነሱት፡፡

ማዕከሉን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሚያስፈልግ ሲሆን÷ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ እንደሆነ መጠቆሙን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.