ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው በኒውካስል ዩናይትድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሐ-ግብር ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው በኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ30 በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኒውካስልን የማሸነፊያ ግቦች አንቶኒ ጎረድን እና አሌክሳንደር አይሳክ ሲያስቆጥሩ ዶሚኒክ ሶላንኬ የቶተንሃምን ማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡
መርሃ-ግብሩ ሲቀጥል ከደቂቃዎች በኋላ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቦርንማውዝ ከኤቨርተን፣ አስቶን ቪላ ከሌስተር፣ ክሪስታል ፓላስ ከቸልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም እንዲሁም ሳውዝሃምፕተን ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወታሉ።
በዕለቱ የሚጠበቀው ሌላው ጨዋታ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ከብራይተን ምሽት 2፡30 የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው።