Fana: At a Speed of Life!

በይዞታቸው ላይ ለማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ፍቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በይዞታቸው ላይ ለማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ፍቃድ ሰጠ።

ቢሮው በ16 ነጥ 75 ሄክታር መሬት ላይ የማልማት ጥያቄ ላቀረቡ አርሶ አደሮች ፍቃድ የሰጠ ሲሆን አርሶ አደሮቹ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት በዛሬው እለት ውል ፈጽመዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ በማኑፋክቸሪንግ፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በሪል እስቴት እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፎች ለመሰማራት ጥያቄ አቅርበው በቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፕሮጀክታቸው ታይቶ እንዲያለሙ ተፈቅዶላቸዋል።

በቀጣይም ቢሮው ተመሳሳይ የማልማት ጥያቄ የሚያቀርቡ አርሶ አደሮችን ጥያቄ ለማስተናገድ ቁርጠኛ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

አርሶ አደሮች በራሳቸው ይዞታ በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲያለሙ በህግ በተደነገገው መሰረት ተደጋጋሚ የሆነ የማልማት ጥያቄ ሲያነሱ መቆየታቸው ይታሳል።

በሰአዳ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.