Fana: At a Speed of Life!

በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ ዛሬ ምሽት 2:01 ሰዓት ላይ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ በአካባቢው የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነው፡፡

ዛሬ ምሽት 2:01 ሰዓት ላይ በፈንታሌ ዙሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 3 እንዲሁም ቀን 11:27 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት በተከታታይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ሰሞኑን ከታዩት ሁሉ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ በመሆኑ ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል እንዲደረግም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በየሻምበል ምኅረት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.