Fana: At a Speed of Life!

ፋና ሀገርና ህዝብን የሚጠቅሙ ስራዎች መስራት አለበት – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ወቅቱ የሚፈልገውን አቅምና ብቃት ተላብሶ ሀገር እና ህዝብን የሚጠቅሙ ስራዎች መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወቅቱ እንዳሉት፤ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሁለት ጠንካራ ሚዲያ ድምር በመሆኑ ወቅቱ የሚፈልገውን አቅምና ብቃት ተላብሶ ሀገርና ህዝብን የሚጠቅም ስራዎች መስራት አለበት።

ያለውን አቅም አሟጦ በመጠቀም የተሻለ እንዲሰራ አቅጣጫ የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመንግስት ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በዛሬው ጉብኝትም ሊጠናከሩ የሚገቡ ውጤታማ ስራዎች መኖራቸውንና ድጋፍ የሚሹ ጥረቶች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ነው ያሉት፡፡

ተቋሙ በዘመናዊ መሳሪያዎች እና በጥራት የተደገፉ ተግባራትን የሚያከናውን መሆኑ ከዚህ ቀደም በሚያቀርባቸው ስራዎች ይታወቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬም ያየነው ይህንኑ ነው ብለዋል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጣይ ዜናና ወቅታዊ፣ የምርመራና ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን ከተገቢ መረጃዎች ጋር ተደራሽ ለማድረግ ስራዎችን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዳንኤል ክብረት በበኩላቸው፤ የዋልታና ፋና ውህደት የመደመር ተምሳሌት መሆን በሚችል ደረጃ ሰፊ ጥናት ተካሄዶ የተፈጠረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ሚዲያው ለሌሎችም ሆነ ቀጣይ ለሚፈጠሩ መገናኛ ብዙሃን ጭምር መጥቀም የሚችል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በኃይለኢየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.