Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሩህነት ፕሮግራም ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ብሩህ ጉዞ” በሚል ስያሜ በቻይና መንግስት ድጋፍ የሚተገበረው የኢትዮጵያ ብሩህነት ፕሮግራም ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ፣ ቲያንጂን የዓይን ሆስፒታል ፕሬዚዳንት ዛንግ ዌይ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ለጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል የ40 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ርክክብ የፊርማ ስነስርዓትም በመርሐ ግብሩ ላይ ተካሂዷል፡፡

12 አባላት ያሉት የቻይና ዶክተሮች ልኡክ ለአንድ ወር በሚቆይ አገልግሎት ለ500 የዓይን ህሙማን ህክምና ለመሥጠት መታቀዱ በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል።

ከነዚህ ውስጥ 80 ህሙማን የተሳካ ቀዶ ጥገና እንዳደረጉና ፕሮጀክቱም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሁኔታዎች ወደማይናወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት ስለመሸጋገሩ ማሳያዎች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የኢትዮ ቻይናን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለውም ተመላክቷል።

በመሳፍንት ብርሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.