ድርጅቱ ለገና በዓል 4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳት ማዘጋጀቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለገና በዓል ጤናማነቱ የተረጋገጠ የዕርድ አገልግሎት ለመሥጠት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።
በዚህ መሰረትም ለበዓሉ የበግ፣ የፍየል እና የበሬ ስጋ ለማኅበረሰቡ በተመጣኝ ዋጋ ለማዳረስ ዝግጅት መደረጉን የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አታክልቲ ገ/ሚካኤል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ድርጅቱ ለገና በዓል 3 ሺህ የቀንድ ከብት እንዲሁም 1ሺህ ፍየልና በግ በላይ ለእርድ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ለበዓሉ ጤናማነቱ የተረጋገጠ የዕርድ አገልግሎት ለመሥጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንም አንስተዋል።
በመላኩ ገድፍ