Fana: At a Speed of Life!

ኢንዶ ገልፍ በኢትዮጵያ በማዳበሪያ ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንዱ ኢንዶ ገልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ በግብርና ኬሚካልና ማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡

በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍሰሃ ሻወል ከሕንዱ የኢንዶገልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳንጃይ አጋርዋል ጋር በኢትዮጵያ የግብርና ኬሚካልና ማዳበሪያ ማምረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ አምባሳደር ፍሰሃ ሻወል÷ በኢትዮጵያ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ የተከናወነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና በፋይናንስ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ለባለሃብቶች አማራጭ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እና በአግሮ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ያሉትን አዋጭ የኢንቨስትመንት እድሎች ለባለሃብቶቹ አስረድተዋል።

በዚህም በሕንድ በአግሮ ኬሚካልና ማዳበሪያ ምርት ቀደምት የሆነው ኢንዶጎልፍ ክሮፕሳይንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው መግለጹን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.