Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቀጣናው መረጋጋትን ለማስፈን በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ ጋር  ውጤታማ ውይይት ያደረገ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንቱ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል።

በውይይቱ ሀገራቱ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (AUSSOM) ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

የሁለትዮሽ ትብብራቸውንም ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የጉብኝት ልውውጦች ለማጠናከርና በቅርቡ የሶማሊያ ከፍተኛ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ  ውይይት ለማካሄድ ተስማምተዋል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብድርቋድር ኑር ጃማ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሰላም ለማረጋገጥ ለከፈለው መስዋትነትና ላበረከተው አስተዋጽዖ ያላቸው አክብሮት እና ምስጋና ገልጸዋል።

አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያላት ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ሽብርተኝነትን መዋጋት የሁለቱ ሀገራት ቁልፍ የትብብር ማዕከል መሆን እንደሚገባውም አስምረውበታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም መሆኑን ገልጸው፤ የቀጣናው የጸጥታ ችግር የልማት አጀንዳዎች ላይ እንዳያተኮር ማድረጉን እንደገለጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.