Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር(ዶ/ር) ከፓኪስታን የፕላን፣ ልማት እና ልዩ ተነሳሽነት ሚኒስትር አህሳን ኢቅባል ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ስለተመዘገበው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ የውጭ ግንኙነትና የማህበራዊ ዘርፎች ዋና ዋና ማሻሻያዎች ለሚኒስትሩ አብራርተዋል።

መንግስት ጎረቤት ተኮር አብሮነት ላይ የተመሠረተ የሠላም ደሴት መፍጠር መቻሉን አምባሳደሩ መናገራቸውን ነው በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ የተመላከተው፡፡

በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ የሚገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር በሀገሪቱ ውስጥ የተደረጉ ማሻሻያዎች ውጤት እንደሆነም አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሚኒስትሩ አህሳን ኢቅባል ÷ኢትየጵያ በአፍሪካ ውስጥ ታላቅ የስኬት ምሣሌ መሆኗንና ብዝሃነት ባለው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች እንዲሁም በንቁ አመራር አማካኝነት ኢኮኖሚዋን መቀየሯን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በለውጥ አመራሩ ሥር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ያጋጠሟትን ችግሮች በመፍታት ያስመዘገበችውን ከፍተኛ የብልፅግና ጉዞም አድንቀዋል።

በቀጣይም ሀገራቱ በልማትና በልዩ ልዩ ተነሣሽነቶች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.