በቱኒዚያ በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ27 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቱኒዚያ ምሥራቃዊ የባሕር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ የ27 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የመገልበጥ አደጋው በሁለት ጀልባዎች ላይ የደረሰ ሲሆን÷ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 27 ስደተኞች ሲሞቱ 83 ሰዎችን ማዳን መቻሉ ተገልጿል።
አደጋ የደረሰባቸው ጀልባዎች ከሰሀራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት መነሻቸውን ያደረጉ ስደተኞችን አሳፍረው ሲጓዙ የነበሩ መሆናቸውን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች እንደገለጹት ፥ ከተገኙት የስደተኞች አስከሬን በተጨማሪ የጠፋ ሊኖር ስለሚችል ፍለጋው እንደቀጠለ ነው።
መዳረሻቸውን አውሮፓ የሚያደርጉ ስደተኞች በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በሚደርሰው ተደጋጋሚ አደጋ ሕይወታቸው ይቀጠፋል።