Fana: At a Speed of Life!

ለጤና ተቋማት የ19 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሕክምና ግብዓት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኙ ጤና ተቋማት ከ19 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ግብዓት ድጋፍ አድርጓል፡፡

በማህበሩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ሸጋው ከፋለ÷የሕክምና ግብዓቱ ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገዛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉ አልትራሳውንድ፣ ማይክሮስኮፕ፣ የህጻናት ማሞቂያ፣ ከባክቴሪያ ነጻ ማድረጊያ፣ የቀዶ ሕክምና እና የተለያዩ መሳሪያዎችን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡

የዞኑ ም/አስተዳዳሪ አጉማሴ አንተነህ በበኩላቸው÷ማህበሩ የጤና ተቋማትን የሕክምና ግብዓት ችግር ለማቃለል ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በጸጥታ ችግር የዞኑ ጤና ተቋማት ከፍተኛ የሕክምና ግብዓት እጥረት እንዳለባቸው ጠቁመው ÷አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በሰለሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.