Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦት ጥያቄ ላቀረቡ ሀገራት ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ለመሆን ጥያቄ ላቀረቡ ሀገራት ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር)÷በሃይል ልማትና ተደራሽነት እንዲሁም ቀጣናዊ ተጠቃሚነትን ረገድ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በእስካሁኑ ሒደት ከጎረቤት ሀገራት ሱዳን፣ ጅቡቲና ኬንያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውሰው÷ በቅርቡ በኢትዮ-ኬንያ በተዘረጋው መስመር ለታንዛንያ የሃይል አቅርቦት የሙከራ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከምታመነጨው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሃይል 90 በመቶውን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በማዋል 10 በመቶውን ደግሞ ለተለያዩ ሀገራት እያቀረበች መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

በቀጣይም የሃይል ልማትና ተደራሽነት ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ÷በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ በኩል ከኢትዮጵያ የኃይል ተጠቃሚነት ጥያቄ መቅረቡን አንስተዋል፡፡

ለቀረበው ጥያቄም ጥናት ተደርጎ እና የሃይል ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ግንባታ ሲከናወን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሦስት ወራት ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.