Fana: At a Speed of Life!

ኃይሌ ሪዞርት በጅማ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ኃይሌ ሪዞርት በጅማ ከተማ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገ/ ስላሴ ÷ ሪዞርቱ በ1 ዓመት ከ 8 ወር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁን ገልፆ ለሪዞርቱ በፍጥነት መጠናቀቅ የጅማ ህዝብ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር ፥ ሪዞርቱ ጅማን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪ የሪዞርቱ በፍጥነት መጠናቀቅ ሌሎች ባለሃብቶችንም እንደሚያነቃቃ ከንቲባው ገልፀዋል፡፡

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር በበኩላቸው ፥ አትሌት ኃይሌ ገ/ ስላሴ በኢንቨስትመንት ዘርፍ እየሰራ ያለው ስራ እንደ ሩጫው ሁሉ ሀገርን የሚያኮራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሪዞርቱ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለከተማውና አካባቢው ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩ ተመላክቷል።

በሙክታር ጠሃ እና አሚና አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.