Fana: At a Speed of Life!

የጤና አገልግሎቱን ለማሳደግ የዳያስፖራው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስገነዘቡ፡፡

የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ለሱልጣን ሼክ ሀሰን የበሬ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ሕክምና ማዕከል 15 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ድጋፉንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ማስረከባቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

በክልሉ የጤና አገልግሎትን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ዳያስፖራው እያከናወነ ላለው ድጋፍ አቶ ሙስጠፌ አመሥግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.