ከባሕርዳር ወደ ላሊበላ የቀጥታ በረራ ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከባሕርዳር-ላሊበላ እና ከላሊበላ-ባሕርዳር የቀጥታ በረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላከተ፡፡
የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አበበ እምቢአለ ለፋና ዲጂታል እንዳረጋገጡት÷ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ታሕሣሥ 28 ቀን 2017 ከባሕርዳር ወደ ላሊበላ የቀጥታ በረራ አለ፡፡
እንዲሁም ታሕሣሥ 29 ቀን 2017 ከላሊበላ ወደ ባሕርዳር የቀጥታ በረራ እንደሚሰጥ አየር መንገዱ አረጋግጦልናል ብለዋል፡፡
ይህ በረራ መዘጋጀቱ በርካታ ጎብኝዎችን የገና (ልደት) በዓል በልዩ ድምቀት ወደ ሚከበርባት ላሊበላ በማመላለስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው እና ይህም ዘርፉን ለማነቃቃት እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡