ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፈነ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጋ መስኖ ልማት ሥራ እስከ አሁን ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር በላይ በዘር መሸፈኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዘንድሮው የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር በላይ በማልማት 173 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እስከ አሁንም ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር በላይ መታረሱን እና ከዚህ ውስጥ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር የሚልቀው በዘር መሸፈኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ሀገራዊ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ በሁሉም ክልሎች የበጋ መስኖ ልማት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡