Fana: At a Speed of Life!

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ቡድን ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የዓለም አቀፉ የስፖርት ፕሬስ ማህበር (ኤአይፒኤስ) የ2024 የዓመቱ ምርጥ ቡድን ሽልማትን አሸነፈ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በ111 ሀገራት ከሚገኙ 518 ጋዜጠኞች በተሰበሰብ ድምፅ በአጠቃላይ 579 ነጥቦችን በማግኘት ሽልማቱን አሸንፏል።

የዩሮ 2024 አሸናፊው የስፔን ብሔራዊ ቡድን 552 ድምፆችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ የ2024 የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ደግሞ 532 ነጥቦችን በመያዝ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ፣ አንሄለል ዲማሪያ፣ ሮዴርጎ ዲ ፖል፣ ጁሊያን አልቫሬዝ፣ ፓብሎ ዲያባላ፣ ኤሚሊ ማርቲኔዝ እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ የመሳሰሉ ከዋከበቶችን ያከተተው የአርጅንቲና ቡድን የ2022 የአለም ዋንጫ ሻምፒን መሆኑ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ ኮሎምቢያን በማሸነፍ የ2024ቱን የኮፕ አሜሪካ ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡

አሜሪካዊቷ የጂምናስቲክ አትሌት ሳይመን ቢልስ እና ስዊድናዊው የምርኩዝ ዝላይ አትሌት አርማንድ ዱፕላንትስ የ2024 የኤአይፒኤስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማትን ያሸነፉ አትሌቶች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.