ዩክሬን ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚተላለፈውን የሩሲያ ጋዝ አቋረጠች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቀርበው የሩሲያ ጋዝ በዩክሬን የጋዝ ማመላለሻ ኦፕሬተር ናፍቶጋዝና በሩሲያ ጋዝፕሮም መካከል ያለው የአምስት ዓመት ስምምነት ማብቃቱ ተሰምቷል፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፥ በመሬታችን ሩሲያ ተጨማሪ ቢሊየን ዶላር እንድታገኝ ሀገራችን አትፈቅድም ብለዋል።
በመሆኑም የጋዝ መተላለፊያውን ዩክሬን ከመዝጋቷ በፊት የአውሮፓ ህብረት እንዲዘጋጅ አንድ ዓመት ሰጥታ እንደነበር አስታውሰዋል።
የአውሮፓ ኮሚሽን ፥ የአህጉሪቱ የጋዝ ስርዓት “ችግርን የሚቋቋም እና ተለዋዋጭ” እንዲሁም በዩክሬን በኩል የሚደረገውን የስምምነት ማብቃት ለመቋቋም የሚያስችል በቂ አቅም እንዳለው ገልጿል።
ሆኖም ሩሲያ አሁንም ወደ ሃንጋሪ፣ ቱርክ እና ሰርቢያ ጋዝ የምትልክ ሲሆን በቱርክ የነዳጅ መተላለፊያ መስመር በጥቁር ባህር በኩል መላክ ትችላለች ነው የተባለው።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው፥ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ከፍተኛ ስቃይ ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡
እንደቢቢሲ ዘገባ በፈረንጆቹ 2022 የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚገባውን የጋዝ አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡
ሆኖም በርካታ የምስራቅ አውሮፓ አባል ሀገራት አሁንም በአቅርቦቱ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ተነግሯል።
ሩሲያ ጋዝ ወደ በማስተላለፍ በዓመት 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ታገኛለች፡፡
በ2023 የአውሮፓ ህብረት ወደ አባል ሀገራቱ ከሚያስገባው ጋዝ መካከል የሩሲያ ድርሻ ከ10 በመቶ ያነሰ ነበር።