Fana: At a Speed of Life!

ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን በላይ ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዘርፉ ባለፉት አራት ወራት 479 ሺህ 830 ቶን በላይ የተለያዩ ምርቶችን በመላክ የእቅዱን 132 ነጥብ 37 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡

አፈጻጸሙ ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ947 ነጥብ 36 ሚሊየን ዶላር ወይም 89 ነጥብ 18 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ከአጠቃላይ ገቢው ግብርና 53 ነጥብ 25 በመቶ ድርሻ ሲይዝ÷ማዕድን 37 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ 5 ነጥብ 43 በመቶ እንዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች 4 ነጥብ 33 በመቶ ድርሻ መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡

ወርቅ፣ ቡና፣ ኤሌክትሪክ እና የጥራጥሬ ምርቶች በገቢም ሆነ በመጠን ከዕቅዳችው በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ምርቶች መሆናቸውን የሚስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

150 ነጥብ 35 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ 674 ነጥብ 55 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን ÷ 9 ነጥብ 03 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት በማድረግ 735 ነጥብ 65 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.