ብሬንትፎርድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛ ሣምት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ መርሐ-ግብር ብሬንትፎርድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ30 ላይ በጌቴክ ኮሙኒቲ ስታዲዬም በሚደረገው ጨዋታ አርሰናል በሊጉ ጠንካራ ከሆነው ብሬንትፎርድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
ጉዳት ላይ የነበረው የብሬንትፎርድ ግብ ጠባቂ ማርክ ፍሌከን በዛሬው ጨዋታ እንደሚሰለፍ ተገልጿል፡፡
በአርሰናል በኩል ከመድፈኞቹ ቁልፍ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ በስተቀር ሁሉም የቡድኑ ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች ዝግጁ መሆናቸውን ክለቡ አስታውቋል፡፡