Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የወጣቶችን አጀንዳ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዋይ ቡንቱ ዩዝ ፒስ ቢዩልዲንግ አሊያንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወጣቶች ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሰስረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎና እና ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) አጀንዳዎቹን ተረክበዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ወጣቶች የጋራ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ኮሚሽነሮቹ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ከሀገራዊ ችግሮቻችን መወጫ ቁልፍ ሚና ላለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ወጣቶች ወሳኝ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም ጥሪ ማቅረባቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.