አሜሪካ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ጦር በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ፡፡
ጦሩ በአማጽያኑ ወታደራዊ ማዘዣ፣ የጦር መሳሪያ ማከማቻ እና ፋብሪካ ላይ በርካታ የአየር ጥቃቶች መፈጸሙን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ጦሩ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ በሚገኘው ራዳር ጣቢያ እና በሰባት የሁቲ የመርከብ ሚሳኤሎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ማድረሱ ተሰምቷል፡፡
ትናንት እና ዛሬ በሰነዓ ከተማ የደረሰው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት በአየርና መርከብ የታገዘ እንደነበርም ተነግሯል፡፡
የሁቲ አማጽያን በተገባደደው የፈረንጆቹ ታሕሣሥ ወር መጀመሪያ ላይ እስራኤልን በባሊስቲክ ሚሳኤል ከመታ በኋላ አሜሪካ እና እንግሊዝ በአረቡ ሀገራት ላይ የቦምብ ጥቃት ማድረስ መቀጠላቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡