Fana: At a Speed of Life!

አዋጁ የጤና አገልግሎትና አስተዳደርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ የጤና አገልግሎትና አስተዳደርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ።

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን አፅድቋል፡፡

 

ሚኒስትሯ በአዋጁ ዙሪያ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት÷ አዋጁ የጤና ተቋማት ዓለም ዓቀፋዊ ሁኔታን ያገናዘበ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችላቸውና ተደራሽነትንም የሚያሳድግ ነው፡፡

 

አዋጁ አዳዲስ የጤና አገልግሎት ስርዓቶች እንዲዘረጉ የሚፈቅድ ድንጋጌዎችን የያዘ፣ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም ባለሙያዎች ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ ክትትልና ቁጥጥር እንዲኖር የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

 

እንዲሁም በርካታ ዜጎች አዳዲስና ዘመኑን የሚመጥን አገልግሎት ፍለጋ ወደ ሌሎች ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር ይሆናልም ነው ያሉት።

 

 

በማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.