ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በቀድሞው የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በቀድሞው የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ተገኝተው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም ለህንድ መንግስት እና ህዝብ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።
ሲንግ ባለራዕይና ድንቅ የሀገር መሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡
ማንሞሃን ሲንግ የኢትዮጵያ እና የህንድን ትስስር አጠናክረው ማስቀጠላቸውንም ጠቅሰዋል ፡፡
ማንሞሃን ሲንግ ባለፈው ሳምንት በ92 ዓመታቸው ማረፋቸው ይታወሳል፡፡