Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የሕክምና ቁሶችን በድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አይ ሲ አር የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሶችን በድጋፍ አበረከተ፡፡

የጋምቤላ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት÷ ድጋፉ በሆስፒታሉ ያለውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ያግዛል።

ለተደረገው ድጋፍ አመሥግነው÷ ሌሎች ድርጅቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ድጋፉ ለህሙማን ተኝቶ መታከሚያ የሚያገለግሉ 40 አልጋዎችን ጨምሮ የሕንጻ ግንባታን ማካተቱም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.