ዋይኒ ሩኒ ከፕሌይ ማውዝ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዋይኒ ሩኒ ከእንግሊዝ ሻምፒየን ሽፑ ቡድን ፕሌይ ማውዝ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል፡፡
የ39 ዓመቱ የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ኮከብ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሩኒ÷ በተደረጉ 23 የቻምፒየን ሽፕ ጨዋታዎች 4 ጊዜ ሲያሸንፍ በ13ቱ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
በአሰልጣኝነት ዘመኑ ስኬት የራቀው ዋይኒ ሩኒ የፕሌይ ማውዝ አሰልጣኝ ከመሆኑ በፊት÷ ከበርሚንግሃም ሲቲ በውጤት ቀውስ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ክለብ በሆነው ዲ ሲ ዩናይትድን ጨምሮ በአሰልጣኝነት በተሳተፈባቸው ቡድኖች ሁሉ ውጤት አልባ እየሆነ ሲሰናበት መቆየቱን ጠቅሶ ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡