Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲያችን ልንቀይራቸው ከማንችላቸው ታሪኮች ጋር ፈፅሞ ፀብ የለውም- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፓርቲያችን ብልፅግና ትናንት የሥርዓተ-መንግሥት አሥተዳደራችን አንድ አካል ሆነው ካለፉ ልንቀይራቸው ከማንችላቸው ታሪኮች ጋር ፈፅሞ ፀብ የለውም ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

በመርህ ደረጃ ከትናንት ተምሮ፣ ዛሬን አሳምሮ፣ ነገን የተሻለ ማድረግን በማመን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በመትጋት ላይ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት እድሳት አቧራን አራግፎ ዐሻራን የማኖር ሥራም በዚሁ እሳቤ የተቃኘ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ጥበብ እና ኢትዮጵያ፤ ስልጣኔ እና ኢትዮጵያ፤ ኅብረ-ብሔራዊነት እና ኢትዮጵያ፤ ቀደምትነት እና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ በልኳ ተሰፍተው ስሟ ሲጠራ አብረው የሚነሱ ተቀፅላዎቿ መሆናቸውን በስፍራው የተሰደረው መኪናውም፣ የንግስና ካባውም፣ ዙፋኑም እና የተለያዩ የሀገራችንን አከባቢዎች የሚገልፁ ስጦታዎችና ሌሎች መገለጫዎች ይመሰክራል ብለዋል።

ትናንት ታሪክ ነው! ዛሬ ቅርስ ነው! ነገ ውርስ ነውና ዕይታችንን ልዕልና መር ጉዞ ላይ በማድረግ ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንትጋ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.