የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቅቋል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ከውይይቶቹ በመነሳት የተለያዩ ውሳኔዎች እንዳሳለፈ እና አቅጣጫዎችንም እንዳስቀመጠ የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡