ኤ ሲ ሚላን ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት አነሳ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ሴሪ ኤው ክለብ ኤ ሲ ሚላን አሰልጣኝ ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ክለቡ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኤ ሲ ሚላን በትናንትናው ዕለት ከሮማ ጋር አንድ አቻ ከተለያየ በኋላ ነው፡፡
በሴሪ ኤው እንዲሁም በአውሮፓ መድረክ ቡድኑ እያስመዘገበ ያለው ደካማ እንቅስቃሴ ለስንብቱ ምክንያት መሆኑም ተገልጿል፡፡
ፓውሎ ፎኔስካ የቀድሞውን የቡድኑ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን በመተካት የማሰልጠን ኃላፊነቱን መረከባቸው ይታወሳል፡፡
ሆኖም ቡድኑ በውድድር ዓመቱ እያስመዘገባ ባለው ደካማ ውጤት ምክንያት ከ6 ወራት ቆይታ በኋላ ለመሰናበት ተገድደዋል፡፡
ፎኔስካን ተክተው የፖርቶ የቀድሞ አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሲሳዎ የኤ ሲ ሚላን አሰልጣኝ ሊሆኑ እንደሚችሉም ከጣሊያን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ፍንጭ ሰጥተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኤ ሲ ሚላን በሴሪ ኤው ከመሪዎቹ አታላንታ እና ናፖሊ በ14 ነጥብ በመራቅ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡