አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር ከዚምባብዌ ጋር በጥር ወር መጀመሪያ ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት ነው፡፡
በዚሁ መሠረት ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ ጀምሮ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው ሽታዬ ስዊት ሆቴል ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ መቅረቡን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡