Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻን በይፋ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐግብሩ የከተማው ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ፣ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሐይማኖት መሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ዶክተር ዮሐንስ ጫላ÷የማህጸን በር ካንሰር በሽታ በሴቶች ብሎም በማህበረሰቡ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመረዳት እና ችግሩን መከላከል ይቻል ዘንድ አስተዳደሩ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በዘመቻው 177 ሺህ 933 ታዳጊ ሴት ልጆች ክትባቱን እንዲወስዱ መታቀዱን እና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በየክፍለ ከተማውና ጤና ጣቢያዎች በበቂ መጠን መድረሱም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም 381 የክትባት ቡድኖችን በማዋቀር በትምህርት ቤቶችና ከትምህር ቤት ውጭ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት እድሜቸው ከ9 እስከ 14 አመት ለሆኑ ሴቶች ክትባቱ እንደሚሰጥ መገለፁን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.