Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ግጥሚያ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ኦልድትራፎርድ ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል፡፡

ጨዋታው ምሽት 5 ሠዓት ላይ ሲደረግ በተደጋጋሚ ሽንፈት ጫና ውስጥ የሚገኘው የሩበን አሞሪም ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

በቀያይ ሰይጣኖቹ በኩል ጨዋታውን ከባድ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል የመሃል ሜዳ ተጫዋቾቹ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ  እና ማኑዌል ኡጋርቴ በቅጣት አለመሰለፋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ቪክቶር ሊንዶልፍ፣ ማሰን ማውንት እና ሉክ ሾው በጉዳት ምክንያት ዛሬ ለቡድኑ አገልግሎት አለመስጠታቸው ተረጋግጧል፡፡

በአንጻሩ በኒውካስል ዩናይትድ በኩል የቀኝ መስመር ተከላካዩ ቲኖ ሊቭራሜንቶ ከጉዳት ይመለሳል፡፡

ሌሎች የዛሬ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ በተመሳሳይ 4 ሠዓት ከ45 ላይ በቪላ ፓርክ

ፓርክ አስቶንቪላ ብራይተንን ሲያስተናግድ÷ ፖርትማን ሮድ ላይ ደግሞ ኢፕስዊች ታውን ከቼልሲ ጨዋቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በ45 ነጥብ ሲመራ÷ ባልተጠበቀ መንገድ ክስተት የሆነው ኖቲንግሃም ፎረስት በ37 ሁለተኛ እንዲሁም አርሰናል በ36 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.