Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪዎቹ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሀና ማርያም ቀለበት አካባቢ የተለያዩ ሰርተፍኬቶችን በማዘጋጀት ሲያሰራጩ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ሀሰተኛ ሰነዶችን እና ሰርተፍኬቶችን የሚያዘጋጁባቸው ቁሳቁሶችና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

ህብረተሰቡ የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት የኢትጵያን ፌደራል ፖሊስ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ EFPapp በመጠቀም መረጃ በምስል፣ በቪዲዮ እና በፅሑፍ በመላክ ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.