ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ቅድመ ሁኔታዎቿን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባት አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ግጭት በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ በዚህ ወቅት የግጭቱን መነሻ ምክንያት መነሳት እንዳለበት እና ውይይቱም መሬት ላይ ያለውን እውነት ማሳየት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡
ዩክሬን ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነትና የምታገኘውን ድጋፍ አስመልክቶ ገለልተኛነቷን ብሎም ኒውክሌርን ከመታጠቅ ጋር በተያያዘ ስላላት አቋም ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
ይህ የሚሆነውም በሩሲያ ደኅንነት ላይ የኔቶ መስፋፋትን ጨምሮ የምዕራቡ ዓለም የሚፈጥረውን ስጋት ለማስወገድ በማሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የዩክሬን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንድሪይ ኢርማክ ከቀናት በፊት ምዕራባውያን በቂ ድጋፍ እያደረጉልን ስላልሆነ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ አይደለንም ማለታቸውን አስታውሶ የዘገበው ዥኑዋ ነው፡፡