Fana: At a Speed of Life!

የቤተ-መንግሥት ሙዚየም ለጉብኝት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤተ-መንግሥት ሙዚየም ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የታላቁ ቤተ-መንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው ሲል ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተጀመረው የእድሳት ሥራ አንድነት ፓርክ ከሆነው ከታላቁ ቤተ-መንግሥት ጀምሮ ይህን እምርታዊ ስፍራ እንደገና ለታላቅ አገልግሎት እንዲሰናዳ በማድረግ ቀጥሏል ሲልም ገልጿል።

ታላቁ ቤተ-መንግሥት አሁን የሕዝባችንን ጽናት፣ ጥበባዊ አቅምና ርዕይ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበት የሀገራዊ ጉዟችን ዋቢ ሆኖ ይታያል ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፡፡

የቀደመ ግዝፈቱንና ውበቱን በመመለስ ያለፈ ታሪካችንን እናከብራለን ሲልም በአጽንኦት ገልጿል፡፡

ለትውልዶች የኩራትና የተነሳሽነት ዘላቂ ተምሳሌት አኑረናል ያለው ጽሕፈት ቤቱ÷ የቤተ-መንግሥት ሙዚየም ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.