Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኮሪያ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 176 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኮሪያ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ላይ በደረሰ አደጋ የሟቾች ቁጥር 176 መድረሱ ተገለጸ።

175 መንገደኞችንና 6 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ከታይላንድ ባንኮክ ወደ ደቡብ ኮሪያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር ሌሊት ላይ መከስከሱ ተዘግቧል።

ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የአደጋ ሠራተኞች ሁለት ሰዎችን በሕይወት ማግኘታቸውን እና የ176 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አልጄዚራና ቢቢሲ ዘግበዋል።

አደጋው በተከሰተበት ቦታ የሚከናወነው የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.