የፋና ላምሮት ምዕራፍ 18 የፍጻሜ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት ሶስት ወራት በአስደናቂ ተወዳዳሪዎች ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት የምዕራፍ 18 የፍጻሜ ውድድር ተካሄደ፡፡
ለፍጻሜው የደረሱት ማዕረግ ሀይሉ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ ግሩም ነብዩ እና እዮቤል ፀጋዬ በሶስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከዛየን ባንድ ጋር አቅርበዋል፡፡
በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በዚህ የፍጻሜ ውድድር ላይ አንጋፋው ሙዚቀኛ ዳዊት ጽጌ በተጋባዥ እንግድነት ታድሟል።
ለውድድሩ ፋና ቴሌቭዥን የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት ያዘጋጀ ሲሆን÷1ኛ ደረጃ ለሚይዝ ተወዳደሪ 400 ሺህ ብር ፣ ለ2ኛ ደረጃ 300 ሺህ ብር ፣ ለ3ኛ ደረጃ 200 ሺህ ብር እንዲሁም 4ኛ ደረጃን ለሚያገኝ ተወዳዳሪ የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡
የፍጻሜ ውድድሩ በሁለቱም የፋና ቴሌቭዥን ቻናሎች፣በፋና ኤፍኤም 98.1 እና በክልል ኤፍኤሞች እንዲሁም በፋና የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች በቀጥታ ተላልፏል።