Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ካምፕ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ካምፕ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አመራሩ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በድሬዳዋ የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ካምፕ ግንባታን ጎብኝተዋል፡፡

ግንባታው ለሠራዊቱ ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠር የግዳጅ አፈፃፀም ስኬታማነትን የሚያሳድግ በመሆኑ ግንባታው በጥራትና በተያዘለት ጊዜ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ስትራቴጂክ አመራሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ መገለጹን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ኮሚሽነር ጀነራሉ በድሬዳዋ በሚገኙ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የቱሪዝም ፖሊስ እና ሌሎች የስራ ቦታዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.