በአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማሕበረሰቡ ለመቀላቀል ያለመ ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በክልሉ ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማሕበረሰቡ መቀላቀልና መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ምክክር አካሂዷል።
ለአተገባበር እንዲረዳም የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዕቅድ፣ የፕሮግራም ይዘት፣ የአተገባበር ስልትና የባለድርሻ አካላት ሚና ምን መሆን አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጎ መግባባት ላይ መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
በምክክሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ የክልሉ እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡