Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለዓይነ ስውራን የመነፅር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ ለ250 ዓይነ ስውራን ዘመናዊ የማንበቢያ መነፅር ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉ 113 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ቀሪዎቹ መምህራን እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው ተብሏል፡፡

መነፅሩ የተለያዩ ጽሑፎችን በካሜራ ቀርጾ ከማስተላለፍ ባለፈ ቀንና ሠዓትንም ጭምር ማሳወቅ ያስችላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.