Fana: At a Speed of Life!

በቦክሲንግ ዴይ የመክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በገና በዓል ሰሞን(ቦክሲንግ ዴይ) የመክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ኤቨርተንን አስተናግዶ 1 አቻ ተለያይቷል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ከ30 በኢቲሃድ በተደረገው ጨዋታ በርናርዶ ሲልቫ ለማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም ኢልማን ኒዲያየ ለኤቨርተን ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው ውሃ ሰማያዊዎቹ  አሸናፊ የሚሆኑበትን የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም ኧርሊግንግ ሃላንድ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

በውድድር ዓመቱ ደካማ አቋም እያሳየ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ 6 የፕሪሚየርሊግ ጨዋታዎችን የተሸነፈ ሲሆን ÷28 ነጥቦችን በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ፉልሃም ቼልሲን 2 ለ 1፣ ኒውካስል አስቶንቪላን 3 ለ 0፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ቶተንሃምን 1 ለ 0 እንዲሁም ዌስትሃም ሳውዝሃምፕተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ቦርንማውዝ  ከክሪስታል ፓላስ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.