Fana: At a Speed of Life!

ተልዕኮውን የተረዳ ጠንካራ ሠራዊት መገንባት ተችሏል – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተልዕኮውን ጠንቅቆ የተረዳ እና ከወገንተኝነት የፀዳ ጠንካራ ሠራዊት መገንባት ተችሏል ሲሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በተቋሙ የተልዕኮ አፈፃፀም እና በቀጣይ መከናወን ስላለባቸው የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአየር ኃይል ክፍሎች ከተውጣጡ የሠራዊቱ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት÷ የተቋሙ የሠራዊት አባላት ተልዕኳቸውን በብቃት እየተወጡ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

አባላቱ ከፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወገንተኝነት ነፃ መሆናቸውን አረጋግጠው፤ ይህም የቆሙበትን አላማ ጠንቅቆ ከመረዳት የሚመነጭ አንዱ የሀገር ፍቅር ስሜት መገለጫ መሆኑን ገልፀዋል።

በሁሉም የተቋሙ ክፍሎች ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ከአመራሩ ጀምሮ በየደረጃው በመግባባት ላይ የተመሰረተ ውስጣዊ አንድነት መኖሩ ለተገኘው ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም የጎላ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት እና ክፍተቶች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ለተቋሙ የለውጥ ጉዞ እንደሚተጉ አመራሮቹ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.