Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 እንደሚካሄድ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

በ1ኛው የብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን በመፈጸም በኩል አበረታች ሥራዎች መፈጸማቸውንም ተናግረዋል።

ባለፈው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ፣ በአሰባሳቢ ትርክት ማዳበር፣ በሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመፈጸም ፓርቲው ለሕዝብ የገባቸውን ቃል በማክበር እና በመፈጸም ላይ እንደሚገኝም አንስተዋል።

በኢኮኖሚው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በተመተግበር ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል።

የአቅም መገንባት ስራዎች መሰራታቸውን አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የማበረታቻ እና የእርምት እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።

የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አንጻርም አበረታች ሥራዎች መሰራታቸውን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርበው የሚነጋገሩበት ምህዳር መፈጠሩን አንስተዋል።

በሂደቱ ያጋጠሙ ከሰላም፣ ከጽንፈኝነት ጋር የተያያዙ እና መሰል ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በመቋቋም ሥኬቶች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል።

ለ2ኛው ጉባኤ ዝግጅትም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በለይኩን አለም

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.